ስነ ምግባራዊ እሴቶችን በመላበስ ብልሹ አሰራርና ሙስናን በመከላከል የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አመራርና አባላት ብርቱ ትግል ማድረግ አለበት ፦ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ

Spread the love

“ስነ ምግባራዊ እሴትን በመላበስ ሙስናን መከላከል ” በሚል መሪ ሀሳብ የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለክልሉ ብልጽግና ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን አመራርና አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና በቦንጋ ከተማ ተሰጥቷል።

የክልሉ ብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት እና የክልሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ብልሹ አሰራርና ሙስናን በጋራ ለመታገል በትብብር ለመስራት የሚያስችል መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

በስምምነቱ መሰረት ለፀረ ሙስና ትግሉ የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ ከሙስና የጸዳች የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሁለንተናዊ ትብብር መስክ በርካታ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል።

ይህንኑ ተግባር ለማሳለጥ የክልሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ታደሰ አይበራ በሰጡት ስልጠና ብልፅግና ፓርቲ ትልቅ ራዕይ እና ትክክለኛ ትልም ይዞ በመፍጠር፣ በመፍጠንና በዝላይ መንገድ አጓጊ ድሎችና ስኬቶች በማስመዝገብ ለሁለንተናዊ ብልጽግና እየተጋ ይገኛል ሲሉ አብራርተዋል።

እነዚህን አጓጊ ድሎችና ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል

በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ አመራርና አባላት በሥነ- ምግባር ግንባታ እና በውስጠ ፓርቲ የፀረ-ሙስና ትግል ላይ በፓርቲ አቋሞችና አቅጣጫዎችላይ የተሟላ ግንዛቤ አግኝተው ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ ስልጠና እንደሆነ ገልጸዋል።

በፓርቲ መዋቅሮች እና በመንግሥት ተቋማት ውስጥ በአግባቡ እንዲወጡ ንቅናቄ ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመቀነስ ግቦች ውስጥ አንዱ የሆነው ሌብነትን መቀነስ መሆኑን የገለጹት ም/ኮሚሽነሩ አመራር አባላት የፓርቲ ሥነ-ምግባር በመላበስና ሌብነትን በመጠየፍ ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል ።

ከኅሊና ቢስነት የሚመነጩ ዝርፍያና ሌብነት የመደመር ቀይ መስመር መሆናቸውን የገለጹት ም/ኮሚሽነሩ እነዚህን ብልሹ አሰራሮችን አመራሩና ባለሙያው በጽኑ አቋም መታገል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የክልሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ የፓርቲውን ተልዕኮ ለማሳካትና ፣የፓርቲውን ፖለቲካዊ ጤንነት ለማስጠበቅ ብልሹ አሰራርና ሙስናን በመከላከል ረገድ የፓርቲ አመራርና አባላት ግንባር ቀደም ሚና ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማሳለጥና ሁለንተናዊ ተቋማዊ አቅም አቀናጅቶ በመረባረብ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን መከላከልና መታገል ተቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለበት አስገንዘበዋል ።

የፀረ ሙስና ትግሉ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ያሉት የክልሉ ብልጽግና ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ሰብሳቢ ወ/ሮ ራሄል ሌዊ ሌብነትን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *