የተፈጥሮ ኃብትን በኃላፊነት የማልማት አይነተኛ ማሳያ የቱሉ ካፒ የወርቅ ፕሮጀክት ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምዕራብ ወለጋ ዞን ገንጂ ወረዳ የሚገኘውን የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክትን ጉኝተዋል።

በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ፕሮጀክቱ የተፈጥሮ ኃብታችንን ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት እንዴት ማዋል እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ መሆኑን ገልጸዋል።

በመንግሥት እና በግል ኢንቨስተሮች ትብብር እየተከናወነ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር የአካባቢውን ማኅበረሰብ የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ በርካታ የልማት ዕድሎችን ይዞ የቀረበ መሆኑም ተመልክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተመለከቱት፣ ፕሮጀክቱ የወርቅ ማምረት ሥራ ብቻ ሳይሆን ለትምህርት፣ ለመንገድ ልማት፣ ለጤና ተቋማት ግንባታና ለዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች መነቃቃት ከፍተኛ አቅም ያለው ነው።

የዚህ ፕሮጀክት ፋይዳ በአንድ ዘርፍ ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ይበልጥ ለልማት በማነሳሳት ረገድ ከፍ ያለ ሚና እንደሚጫወት ያላቸውን ጽኑ እምነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ይህም ተፈጥሯዊ ፀጋዎቻችንን በአግባቡ በማልማት የጋራ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ መሆኑ ተመልክቷል።

#EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *