




በብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አስተባባሪዎች ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚና ደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ፣ዶ/ር ፈለቀች ተክለማርያም ሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚና የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፕላን ቢሮ ምክትልሀላፊ ፣ኢንጅነር ትዕግስት ተረፈ የሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚና የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት ጊምቦ ወረዳ ኡፋ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በአቀባበሉም ስነስርዓት የደቡብ ምዕራብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰበለጸጋ አየለ ፣የጽ/ቤቱ ም/ ኃላፊ ወይዘሮ ዉባለም በዛብህ ፣ የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወይዘሮ እታገኝ ወልዴ ፣ የክልል፣ የዞንና የጊምቦ ወረዳ ሴት አመራሮች እና አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አስፈፃሚዎች በጊምቦ ወረዳ በኡፋ ከተማ በሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ በክንፉ አባላት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ምልከታ አድርጓል ።
