“ኃይልን በማሰባሰብና በመደመር መንገድ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሻገር በሚደረገው ጥረት የመምህራን፣ የግብርናና የጤና ባለሙያዎች ሚና የጎላ ነው” – አቶ ኢብራሂም ተማም

Spread the love

በጨና ወረዳ “ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር!” በሚል መሪ ቃል የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫን አስመልክቶ ከትምህርት አመራሮች ፣ ከቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፤ እንዲሁም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂዷል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊና በዋቻ ምርጫ ክልል ለክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለጹት፤ ብልፅግና ፓርቲ ሀገርን መምራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምህዳር ላይ አዲስ ምዕራፍ የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል ።

በዚህም ውስጥ ሀገሪቱ ከነበረችበት ዘርፈ-ብዙ ችግሮች በመላቀቅ ወደ ተምሳሌታዊ ሀገር እንድትሸጋገር በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

መምህራን የታነጸና የነገ አገር ተረካቢ ትውልድን ከመቅረፅ ባለፈ ለለውጡ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን አቶ ኢብራሂም ተማም ጠቁመዋል ።

ጤናማና አምራች ማህበረሰብ እንዲኖር በማድረግ ረገድም የጤና ባለሙያዎች ድርሻ የማይተካ መሆኑን አብራርተዋል።

የሀገራችን የዕኮኖሚ የጀርባ አጥንት በሆነው በግብርና ዘርፍም የብልጽግና ፓርቲ መንግሥት ልዩ ትኩረት በመሥጠት እምርታዊ ለውጥ እንዳስመዘገበ ገልጸዋል።

ዓላማችንና ግባችን ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ነው ያሉት አቶ ኢብራሂም፥ እንቅስቃሴያችን ከብልፅግና ዕሳቤን ያረጋገጠ እንዲሆን አሳስበዋል።

መጪው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ በብልፅግና አሸናፊነት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የወረዳው ህዝብም ሆነ ምሁራን ለብልፅግና ፓርቲ እያሳየው ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ያሳሰቡት ኃላፊው፥ ግንቦት 24 ብልፅግና ፓርቲ በመምረጥና በማስመረጥ ድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የካፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም በዋቻ ምርጫ ክልል ለክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ አቶ ደመላሽ ንጉሴ በበኩላቸው፥ ፓርቲው ወደ አመራር ከመጣ በኋላ በርካታ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ድሎችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

በብልጽግና ፓርቲ ሕዝብ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካዊ እንዲሁም በሌሎች መሰረተ-ልማቶች በተጨባጭ ተጠቃሚ መሆኑን ተናግረው፥ በቀጣይ ለህዝብ መጥቀም በሚችሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ ፓርቲው በትጋት ማስቀጠል የሚችልበት አቅም ላይ ይገኛል ብለዋል።

የጨና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተረፈ ገ/ማርያም በበኩላቸው፤ በከተማ አስተዳደሩ የተጀመሩ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ የሁሉም ዜጋ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መምህራን፣ ግብርናና የጤና ባለሙያዎች ለተጀመረው የብልፅግና ጉዞ መፋጠን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ መምህራን፣ ግብርናና የጤና ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት፤ ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያከናወናቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች የሀገርን ገፅታና ኢኮኖሚ ከፍ ያደረጉ መሆናቸውን በግንባር ቀደምትነት በመጥቀስ፣ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑና መጪው ምርጫ በስኬት ይጠናቀቅ ዘንድ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ በቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለትም የወረዳው ምሁራን ማለትም መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች፣ የግብናና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች አደባባይ ላይ በመውጣት ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ በአደባባይ ሰልፍ አሳይተዋል ሲል የካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *