በምዕራብ ኦሞ ዞን በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ ዉይይት በጀሙ ከተማ ተካሄደ

Spread the love

በውይይቱ የተገኙት የኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት አመራር ሜጀር ጀነራል ታደሰ አመሎ እንደተናገሩት አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ ላይ አመራሮች እና የፀጥታ አካላት ተቀናጅተው መስራት አለባቸው ብልዋል።

ወቅቱ የምርጫ ከመሆኑም አንጻር የተሳካ ምርጫ ለማድረግ ጠንካራ ሥራዎች እንደሚሰራ ተናግሯል።

የመንግስት አቅጣጫ ተከትልን ስራዎች እንስራለን ያሉት ጀነራሉ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት የሚሰጣቸው ተልዕኮ በብቃትና መወጣት አለባቸው ብልዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ ባይኔዝ አያይዘውም በባለፉት ጊዜያት በተሰራው ሥራ ለዉጦች መኖራቸውን አውስተው ይህ ለማስቀጠል ተጽዕኖ የሆኑት ምክንያቶች ተለይተው መፍታት እንደሚገባ ተናግሯል።

ግንቦት 24 ሀገራዊ ምርጫ የሚደረግበት በመሆኑ በየአካባቢው የሚታየው ችግሮች በፍጥነት መፍትሔ ተበጅቶለት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች ማጠናከር አለበት ብልዋል።

የክልሉ የሠላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ ዓለሙ በበኩላቸው በአርብቶአደር አከባቢዎች አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የእርስ በርስ ዝርፊያ ግዲያ መሰረታዊ ችግሮች ተለይተው በተገቢው መንገድ መስራት እንደሚገባ ተናግሯል።

በየአከባቢዎች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶች መንስኤዎችና አባባሽ ምክንያቶች በመለየት ጠንካራ የህግ ማስከበር ሥራ እና ጠንኳራ የሆነ ተጠያቂነት መሰረት ያደረገ ሥራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ እንደተናገሩት የልማት ስራዎች ስኬታማ ሊሆኑ የሚችሉት አስተማማኝ ሰላም ሲኖር በመሆኑ ለሰላም ቅድሚያ መስጠት አማራጭ የሌለው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ወቅቱ የ7ተኛ ሀገራዊ ምርጫ የቅስቀሳ ሥራ የሚደረግበት በመሆኑ በየአካባቢው በሠላም እና በምርጫ ሥራዎች አመራሮች እና ባለድርሻ አካላዊ ግንባር ቀደም ሚና መወጣት አለባቸው ብልዋል።

መዋቅሮች በሠላም እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ከወትሮው በተለየ መልኩ በመቀናጀት የህዝብ ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት በብቃት መወጣት እንደሚገባው አክሎበታል።

ውጤት ላይ ማተኮር ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪ መዋቅሮች የተሰጣቸው ተልዕኮ መኤኒት ሻሻ ወረዳ ዉጤታማ በመሆኑ ሌሎቻችሁ የአርብቶ አደሮች መበቃቀሎች እንዲቆሙ ጠንኳራ የሆነ ሥራ እና ተጠያቂነት መሰረት ያደረገ ሥራዎች እንደሚሰራ ተናግረዋል።

‎በመድረኩ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ፣የፀጥታ አካላቶች፤ የክልል ፤የዞን ከፍተኛ አመራሮች ፤የሱሪ ወረዳ፤ የቤሮ ወረዳ፤ የማጂ ወረዳ፤ የጎሪ ጌሻ ወረዳ እና የማጂ ቱም ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የፀጥታ አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *