በታርጫ ከተማ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት፣ በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ የታጀበ የብልጽግና ፓርቲ የይምረጡኝ ቅስቀሳ እና የድጋፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት፣ የብልጽግና ፓርቲ የይምረጡኝ ቅስቀሳ እና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ይህ ታላቅ የህዝብ ንቅናቄ የለውጡ መንግሥት ላስመዘገባቸው ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶችና ለህዝብ ተጠቃሚነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልፅግና ይሁንታን የሚሰጥ መኾኑ ተመላክቷል።

የዞኑ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ እያሳየ ያለው ደማቅ ድጋፍ፣ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠል ወደ ላቀ ብልጽግና ለመጓዝ ያለውን ጽኑ ፍላጎት በግልጽ የሚያሳይ ነው።

በለውጡ መንግሥት የተከናወኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎች በዞኑ ውስጥ ለዘመናት ተረስተው የነበሩ የቱሪዝም ሀብቶች እንዲነቃቁና ለህዝብ ጥቅም እንዲውሉ ማድረጉ ይጠቀሳል።

በለውጡ መንግሥት ዕሳቤ የዞኑን የተፈጥሮ ጸጋ ወደ ሃብት በመቀየር ረገድ የከሰል ድንጋይ ማዕድን ማውጣት ሥራ መጀመሩ ሌላው ትልቅ ስኬት ሲሆን ይህም በከርሰ ምድር የተሸሸገ ጸጋ ለሀገር ልማት እንዲውል በማድረግ የዞኑን የኢኮኖሚ አቅም ማነቃቃት ለበርካቶች የሥራ ዕድል የፈጠረ ነው።

ሰልፈኞቹ “በአንድነታችን የኢትዮጵያን ብልፅግና እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ቃል የአብሮነት መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን፥ በአካባቢው እየተመዘገቡ ያሉ የልማት ስራዎችን በማድነቅም “የጀመርናቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች በስኬት ይቀጥላሉ!” በማለት ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም የተጀመሩትንና በቀጣይ የሚከናወኑትን ታላላቅ የልማትና የዲሞክራሲ ስራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል ብልጽግና ፓርቲን ይመርጣል የሚሉ ድምጾችን ሰልፈኞች እያሰሙ ይገኛሉ።

በድጋፍ ሰልፉ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የፓርቲ ዕጩዎችና አባል ደጋፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *