





በዳውሮ ዞን በታርጫ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎችና አባላት ታሪካዊና ልዩ ድባብን የፈጠረ የ”ይምረጡኝ” እና የድጋፍ ሰልፍ በደመቀ ሁኔታ እየተካሄደ ነው
የፓርቲው ደጋፊዎች “ዛርጋ ዶራ!!” (የስንዴ ነዶ ይምረጡ) በሚል ህብረ ዜማ የጋራ ድምጻቸውን አደባባይ እያሰሙ ይገኛሉ።
ይህ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ፓርቲው ላስመዘገባቸው የልማትና የፖለቲካ ስኬቶች ያለውን አጋርነት ለመግለፅና በቀጣዩ ምርጫ ያለውን ድጋፍ ለማሳየት የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
የአከባቢው ማህበረሰቡ ባህሉን፣ አንድነቱን የገለፀበት ይህ መድረክ ብልፅግና ፓርቲ በቀጣይም የጀመራቸውን የለውጥ ጉዞዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ትልቅ አቅምና ስንቅ እንደሚሆን ተመልክቷል።
ሰልፈኞቹ እስከ ምርጫው ዕለትና ከምርጫው በኋላም ከፓርቲው ጎን መቆማቸውን በቁርጠኝነት እያሳዩ ይገኛል።
