






በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ስልፍ ተካሂዷል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ የብልፅግና ፓርቲ አካታች የፖለቲካ ምህዳር መፈጠሩ በመድረኩ የገለጹት።
ፓርቲ ለዓመታት በልማት ተዘንግተውና ወደኋላ ቀርተው የኖሩ አካባቢዎችን ታሪክ በመቀየር የልማት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
በክልሉ ባለፉት አመታት በልማትና በመልካም አስተዳደር ረገድ ይነሱ የነበሩ ችግሮችን መፍታት እየተቻለ መኾኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም ሠላምና ልማት እንዲሁም የኢኮኖሚ አቅም ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
በክልሉ ለተመዘገበው አውንታዊ ለውጦች የኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ የጎላ ድርሻ እንደነበረው የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይም ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎችን ለመመለስ የክልሉ መንግሥት ቁርጠኛ መኾኑን ተናግረዋል።
በክልሉ የመጡ ተጨባጭ ልማትና ለውጦችን በማጠናከር በቀጣይም ሁለንተናዊ ልማት ለማጠናከር ህዝቡ ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
የብልፅግና ፓርቲ የዳውሮ ሕዝብ ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በመሆን ለረጅም ጊዜ ሲያነሳው የነበረው ራስን በራስ የማስተዳደርና በክልል የመደራጀት ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ በሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ እውን መሆኑን ነው የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን የገለጹት።
ይህ ስኬት ፓርቲው የሕዝብን ድምፅ የሚሰማ፣ ተግባራዊ ምላሽ የሚሰጥና የገባውን ቃል የሚያከብር መሆኑን በተግባር ያረጋገጠበት ታሪካዊ ድል መሆኑ ተገልጿል መኾኑንም አቶ ፍቅሬ ገልጸዋል።
ፓርቲው የክልሉን ሕዝብ የዘመናት የመልማት፣ የማደግና የመበልጸግ ፍላጎት እውን ለማድረግም ሁሉ-አቀፍ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ስትራቴጂ በመንደፍ፣ ያሉትን ጸጋዎችና አቅሞች አቀናጅቶ በመምራት መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት መቻሉን እንዲሁ።
በፓርቲው ዕሳቤ፣ ያሉትን የተፈጥሮ ጸጋዎችና አቅሞች በመለየት ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማዋል በነደፈው የብዝኃ-ዘርፍ አገር በቀል ኢኮኖሚ እሳቤ የሕዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሰፋፊና ትውልድ ተሻጋሪ እመርታዊ ውጤቶች መመዝገባቸውንም ሀላፊው ጠቁመዋል።
7ኛውን አገራዊ ምርጫ በተሳካ መልኩ ማካሄድ የዲሞክራሲ ተቋማትን ጥንካሬ በማረጋገጥ የአገረ-መንግሥት ግንባታውን እንደሚያጸናው መኾኑን የገለጹት አቶ ፍቅሬ፤
ይህ ምርጫ ለሁለንተናዊ ብልፅግና መዳረሻ ግብ መሠረት የሆነውን የፖለቲካ መረጋጋትና ቅቡልነት በማረጋገጥ፣ ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይን ለማሳካት ምቹ የፖለቲካ መደላድል እንደሚፈጥርም አብራርተዋል።
በመሆኑም ለዜጎች የክብርና የኩራት ምንጭ የሆነችን ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ኅብረተሰቡ የፓርቲው የምርጫ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ በመምረጥ ብልፅግናን እንዲያሸንፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
በዞኑ በርካታ የልማት ጥያቄዎች በለውጡ መንግሥት ምላሽ ማግኘቱን የገለጹት የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ የመጡ ለውጦች ተጠናክሮ እንዲቀጥል የዞን ህዝብ ከፓርቲ ጎን መኾኑን አረጋግጠዋል።
የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች በነቂስ በመውጣት ላሳዩት ድጋፍ አስተዳዳሪው ምስጋና አቅርበው ግንቦት 24 በሚከናወነው ጠቅላላ ምርጫ የስንዴ ነዶውን እንዲመርጡ አሳስበዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
