በሲዝ ከተማ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የ”ይምረጡኝ” ቅስቀሳ በተለያዩ ሁኔቶች እየተካሄደ ነው

Spread the love

የብልጽግና ፓርቲ በቤንች ሸኮ ዞን በሲዝ ከተማ ”ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በተለያዩ መረሃ ግብሮች ታጅቦ በድምቀት እየተካሄ ነው።

በዚህ በሲዝ ከተማ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በማስመልከት እየተካሄደ ባለው የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የዞን፣ የሼይ ቤንች ወረዳና የሲዝ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የፓርቲው አባላትና ነዋሪዎች ተገኝቷል።

የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፉ ፓርቲው ባለፉት ዓመታት ያስመዘገባቸው ስኬቶችንና የነገ ብሩህ ተስፋ የያዙ መፈክሮችና በተለያዩ መረሃ ግብሮች ታጅቦ በድምቀት በመካሄድ ላይ ነው።

ለአብነትም መንገዳችን መደመር፤መዳረሻችን ብልጽግና ምልክታችን የስንዴ ነዶ፣ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር፣ትናንትን ማከም ነገን መተለም ፣በምርጫችን የወደፊት ዕጣ ፈንታችንን እንወስናለን፣ የብልጽግና ጉዞ በህዝብ ይሁንታ ይቀጥላል፣ምርጫችን ብልጽግና ፓርቲ ነው፤ የምርጫ ምልክቱ የስንዴ ነዶ ነው፣እና በመሳሰሉ መፈክሮች ታጅቦ ነው እየተካሄደ ያለው ሲል የሼይ ቤንች ወረዳ ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *