




“የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በሸካ ዞን የሚገኙ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ጋር ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ የውይይት መድረክ በማሻ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በመክፈቻ ንግግራቸው ሚዲያ በፖለቲካው፣ ኢኮኖሚዊና በማህበራዊ ዘርፎች ውጤታማ ለውጥ እንዲመዘገብ እንዲሁም አካባቢን በማስተዋወቅና መላው ህዝብ የልማት ተነሳሽነቱን እንዲያሳድግ ትልቅ ሚና ተወጥቷል ብለዋል።
ለሀገር ዘላቂ ሰላም፣አንድነትና ብልጽግና መረጋገጥ ሚዲያ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የሚዲያ ባለሙያዎች ሀላፊነታቸውን በመወጣት ለሀገር ሁለንተናዊ ለውጥ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ለውይይቱ ተሳታፊዎች አሁን ለምንገኝበት ዓለምአቀፋዊ እና ሀገራዊ ሁኔታ ላይ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና ከፍተኛ መሆኑን ባቀረቡት ሪፖርት የገለፁት የሸካ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙልጌታ አድራሮ በዘርፉ በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለትካዊ ዘርፎች በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል ።
በውይይት መድረኩ ላይ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ፣ የማሻ ኤፍ ኤም ራዲዮ ተቋምና የሸካ ቴሌቪዥን ሰራተኞች እንዲሁም በዞኑ ካሉት ሁሉም መዋቅሮች የተወጣጡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው ሲል ማሻ ኤፍኤም ዘግቧል።
