




“የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና!”በሚል መሪ ቃል በካፋ ዞን የሚገኙ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና እና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን ሀገራዊ ሰነድ በካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ እሸቱ እየቀረበ ሲሆን በተሳታፊዎች ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ህዝብ ለልማት ለማነሳሳት፣ሀገራዊ አንድነትን ለመፍጠር፣የጥላቻ ሀሳቦችን ለመግራት እና ሌሎችን ችግሮችን ለማረም የሚዲያዎችና ኮሙኒኬሽን ሚና ከፍተኛ መሆኑን መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ኃይሌ ተናግረዋል።
ጊዜ ግለሰቦችና ድርጅቶች እራሳቸውን እንዲገልጹ የሚጠይቅ ነው ካልሆነ የሚሰጣቸውን መገለጫ እንዲቀበሉ የሚያስገድድ እንደሆነ አቶ አጥናፉ ጠቁመዋል ።
ሀገራች ኢትዮጵያ ለውጡን ከተቀበለች ማግስት ግጭት፣ ጦርነት፣ አንበጣ ወረርሽኝ፣ኮቭዲ በሽታ እና መሰል ችግሮች በመቋቋም ችግሮችን በጥበብ በመሻገር አመርቂ ለውጦች መመዝገቡን ገልጸዋል።
አሁን በሀገራች ነጠላ ትርክቶች እየበዙ ነው ያሉት ኃላፊው ሀገርን ለመገንባት አሰባሳቢ ትርክቶችን መከተል ያስፈልጋል ለዚህም የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት ሚና የጎላ ነው ብለዋል።
የመንግሥትን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ዕቅድ እና አፈጻጸም በየደረጃዉ ማሳወቅ ያለበት የሚዲያና ኮመኒኬሽን ዘርፉ በመሆኑ በፍጥነት እና ሳቢ አቀራረብ መቅረብ እንደምገባ አሳስበዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል።
