የማኅበራዊ ልማት ሰጪ መሠረተ ልማት ለማስፋፋት ቅድሚያ ተሰጥተው እየተሰራ ይገኛል – ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ፣የያዶታ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ መሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በስነስርዓቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት የክልሉ መንግሥት የማኅበራዊ ልማት ሰጪ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋት ቅድሚያ ተሰጥተው እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የዜጎችን ኑሮ በተጨባጭ ለመቀየር ይሰራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ከለውጡ በፊት ሰፊ የልማት ክፍተት በነበረባቸው የክልሉ አከባቢዎች ፍትሀዊ ልማት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የሆስፒታሉ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ በጥራት እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ተገቢውን የክትትል ስራ እንዲከናወንም ዶክተር ነጋሽ አሳስበዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ቃልን በተግባር እየገጠ ለህዝቦች የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ ተጨባጭ ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝ በመጥቀስ የሆስፒታሉ መገንባት ፍትሀዊ የጤና አግልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።

የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መገንባት በአከባቢው ከዚህ ቀደም ይነሳ የነበረውን በቅርበት ጥራት ያለውን የጤና አግልግሎት ከማረጋገጥ ባለፈ የክልሉን የጤና ተቋማት ተደራሽነትን የሚያሰፋ እንደኾነ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ገልጸዋል።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ፥ የረዥም ጊዜ የወረዳው ኅብረተሰብ የልማት ጥያቄ ምላሽ እያገኙ እንደኾነ በመግለጽ በቀጣይም ቀሪ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የዞኑ አስተዳደር በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ለህዝቡ የልማት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ የሚደነቅ መኾኑን የገለጹት የሳይለም ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አየለ፥ የተቀሩ ጥያቄዎችም ደረጃ በደረጃ እንደሚፈታ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

የወረዳው አስተዳደር የህዝብ የልማት አቅሞችን በማቀናጀት የልማት ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን ቁርጠኛ መኾኑንም ጨምሮ ገልጸዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *