ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ከ353 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው ሆስፒታል የመሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ፣ የያዶታ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ መሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ከ353 ሚሊዮን በላይ በሆነ የክልሉ መንግሥት የበጀት የሚገነባው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአግልግሎት ክፍት እንደሚኾን ተመላክቷል።

የሆስፒታሉ መገንባት ከዚህ ቀደም በአከባቢው ከጤና ተቋማት ተደራሽነትና ጥራት ጋር ተያይዞ ከኅብረተሰቡ ለሚነሳው የልማት ጥያቄ ምላሽ የሰጠ መኾኑ ተመልክቷል።

በመርሐ-ግብሩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *