የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” በሚዛን አማን ከተማ እየተከበረ ነው።

Spread the love

ቢስት ባር የበኩር እህል የሚቀመስበት፣ጨለማው አልፎ ወደ ብርሃን የሚሻገርበት ወቅት፣ የጥጋብና የደስታ ጊዜ፣ እርቅ የሚፈጸምበት ፣ከአባቶች ምርቃት የሚሰጥበት ፣ፈጣሪያቸውን በጋራ የሚያመሰግኑበት፣ ሰው ያለውን በጋራ ተካፍሎ የሚበላበት ወቅት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሳይበረዝ ሲሸጋገር የቆየ የቤንች ብሔር እሴት ነው።

በዓሉ በሚዛን አማን ከተማ አየር ማረፊያ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል ።

በቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የቤንች ነገስታቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ከየዞኖች የመጡ እንግዶች እየተሳተፉ ነዉ።

የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በቀጥታ በቻናል አንድና ሁለት በቀጥታ እየተሰራጨ ነዉ።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *