




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በመንግሥት ግዥ ንብረት ባለስልጣን ለወረዳ የግዥ ባለሙያዎች በካልም ፕሮግራም በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በቦንጋ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
የክልሉ መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ የሺሃረግ ደበበ ከመንግስት በጀት ከ64% በላይ የሚሆነው በጀት ለግዥ እንደሚውልም ተናግረዋል።
ለግዥ የሚመደበው ውስን በጀት ለታለመለት ዓለማ እንዲውል የግዥ ስርዓቱ ከአድሎኦ የጸዳ፣ አሳታፊ፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት እንዲሆን የግዥ ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ወ/ሮ የሺሃረግ ደበበ በንግግራቸውም የግዥ ኦዲት ሲፈጸም ግኝቶችን መነሻ ባደረገ አኳኋን ሊፈጸም ይጠበቃልም ብለዋል።
በወረዳዎች በካልምና በመደበኛ ግዥ ሂደቶች ላይ በኦዲት ግኝት ወቅት ክፊተቶች እየተስተዋሉ በመሆኑ ክፍተቶችን ማጥበብ እንዲቻል ለግዥ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ማስፈለጉንም አስረድተዋል።
ስልጠናው በመንግስት ግዥ አጠቃላይ ገጽታ ፤የመንግስት ግዥ ትርጉም፣ በግዥ ዓይነቶች፣ ግዥ አላማና መርሆች፣ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነቶች፣ የግዥ ዕቅድና በተፈቀዱ ግዥ ዘዴዎች፣ የጨረታ መገምገምያ መስፈርት፤የውል አስተዳደርና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
የክልሉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን የመንግስት ግዥና ንብረት ኦዲትና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ታምራት ወርቁ ስልጠናው እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል።
በስልጠናው ማጠቃለያ ከ2014 ዓ.ም እስከ 2016 ድረስ በግዥ ኦዲት የተገኘ ግኝት ለተሞክሮ የሚቀርብ መሆኑም ተመላክቷል።
በፍቅር ከበደ
