ለቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ የአመራሮች ምልመላና መረጣ በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋለውን ችግር የሚቀርፉ አመራሮች የሚለዩበት ነው፦ አቶ ማርቆስ ቡልቻ

Spread the love

የቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ የዲንና ምክትል ዲኖች አመራርነት ምልመላና መረጣ መርሃግብር እያካሄደ ነው።

በመርሃ _ግብሩ ተወዳዳሪዎች ለአሸናፊነት የሚያበቋቸውን ስትራቴጂክ ዕቅዳቸውን አቅርበው እያስገመገሙ ነው።

በዚሁ የአመራሮች ምልመላና መረጣ መርሃ ግብር የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የመምህራን ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማርቆስ ቡልቻ ባስተላለፉት መልዕክት ዕውቀት፣ብቃት፣ተነሳሽነትና ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ውድድር መሆኑን ተናግረዋል ።

ውድድሩም ግልጽ ፣ፍትሐዊና አሳታፊ እንዲሆንም ይጠበቃል ብለዋል አቶ ማርቆስ በመልዕክታቸው ።

የቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ በክልሉ ብቸኛ መሆኑንና ወደፊት አሻጋሪ መምህራንን በማፍራት በኩሉም የድርሻቸውን ሲወጣ ቆይቷል ብለዋል።

በ21ኛው ክፍለ ዘመን ወቅቱን የዋጀ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማቶችን በማፋጠን በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋለውን ችግር የሚቀርፉ ተወዳዳሪዎች አሰራርና ስርዓትን በተከተለ መንገድ ምልመላ መከናወኑንም አቶ ማርቅስ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ አመራሮች የስራ ዘመናቸው የተጠናቀቀ በመሆኑ በቀጣይ ጊዜያት ትምህርት ኮሌጁን የሚመሩ አመራሮች በግልጽ ማስታወቂያ ተወዳድረው ተገቢና መስፈርቱን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች መለየታቸውንም ገልጸዋል።

ለቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ ዲንና ምክትል ዲን አመራርነት የተወዳደሩ ዕጩዎች የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚዛን ቴፒና የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ተወካዮች ፣ገምጋሚዎች እና አወዳዳሪ ኮሚቴዎች በተገኙበት ስትራቴጂክ ዕቅዳቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።

ለኮሌጁ ዲን፣ምክትል ዲንና የፋይናንስ አገልግሎት ምክትል ዲንነት የቀረቡ ተወዳዳሪዎች ባቀረቡት ስትራቴጂክ ዕቅድ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችን ተቀብለው በመመለስና በኮሚቴዎች በሚሰጠው ውጤት መሠረት አሸናፊው የሚለይ ይሆናል ።

ፕሮግራሙ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚከናወን መሆኑን ከወጣው የድርጊት መርሃግብር ማወቅ ተችሏል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *