ሀገራዊ ምርጫ የተሳካ እንዲሆን የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሚና የላቀ ነው- ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር)

Spread the love

የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ የዋና ጽ/ቤት እና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አመራሮች በተገኙበት በአዲስአበባ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ ከወራት በኋላ የምታካሂደው 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃና ተምሳሌታዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የላቀ ነው ብለዋል።

በንግግራቸው ኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሂደት ሽግግር ላይ እንደምትገኝ ያብራሩት ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲፀና ትልቁን ሚና ስለሚጫወት ብልፅግና ፓርቲ ለቀጣይ ሀገራዊ ምርጫ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

ምርጫው መላው ዓለም ተምሳሌት የሚያደርገው እንዲሆን ለማድረግ ጠንካራ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራዎች እንደሚሰሩም ገልፀዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ ያስቻሉ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራዎች መከናወናቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ ህበረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር፣ ገዢ ትርክትን ለማጽናት፣ ወንድማማችነትን/እህትማማችነትን የሚያጎለብቱ በርካታ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል።

ዘርፉ ባለፉት ስድስት ወራት በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎች ፓርቲው በተለያዩ መስኮች ያሳካቸውን ድሎች ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ጉልህ ድርሻ ማበርከቱን ጠቅሰው በዚህም የኢትዮጵያን ገጽታ ከፍ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

የዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራዎችን በተጠናከረ መንገድ በመስራት ፓርቲው በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቀጠናውና በአለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ በመፍጠር ተምሳሌታዊ ሚና እየተወጣ መሆኑን ማሳየት መቻሉን ተናግረዋል።

በመድረኩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በዕሳቤ፣ በትጋትና በውጤት የተቀናጀ የለውጥ ስራዎችን መስራት በመቻሉ በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በከተማዋ ስኬታማ ጉዞ ውስጥ የህዝብና ግንኙነት የኮሙዩኒኬሽን ስራዎች የላቀ ሚና አበርክተዋል ብለዋል።

በቀጣይም የህዝብ ግንኙነት፣ የኮሚዩኒኬሽንና የሚዲያ ስራዎችን አቀናጅቶ በመጠቀም የከተማዋን ተምሳሌትነት የሚያጎሉ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚከናወን ይሆናል።

#prosperity

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *