ክልሎች በአጭር ጊዜ መሶብ የአንድ መዐከል አገልግሎት እንዲያደራጁ አቅጣጫ ተቀምጧል፦ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Spread the love

የፌደራል መንግሥት የጀመረውን የአገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ለማሳለጥ እንዲያስችል ተደርጎ የተሰራው መሶብ የአንድ መዐከል አገልግሎት በክልሎችም መቀጠል እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል።

ለዚህም እንዲህ ያለው መዐከል በክልሎችም በፍጥነት እንዲተገበር አቅጣጫ መቀመጡን ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።

በመዐከሉ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ፈጣን እና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን የአገልግሎት አሰጣጥ በራስ አቅም መሰራቱን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ አሰራር ወደክልሎች በአጭር ጊዜ መስፋት አለበት ነው ያሉት።

በፌደራል ደረጃ የተሰራው ዲጂታል ሲስተም በራስ አቅም የተገነባ በመሆኑ ለሌሎችም ተደራሽ ለማድረግ እድሉ መኖሩን ጠቁመዋል።

ለዚህም እያንዳንዱ ክልል ቢያንስ አንድ የአገልግሎት መስጫ መዐከል ማደራጀት እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡን ኢቢሲ ዘግቧል።

ይህን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ክልሎች በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ይህን መሰል መዐከል እንዲያደራጁ ይጠበቃል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *