


በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ በሬ በማደለብ ስራ የተሰማራው ወጣት ውጤታማ መሆኑን ገለጸ
በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ ካንጋ ቀበሌ በሬ በማድለብ ለገበያ የሚያቀርበው ወጣት በላቸው ጋጪቶ ውጤታማ መሆኑን ገልጿል።
ወጣት በላቸው ጋጪቶ እንደተናገሩት ከብት ማድለብ ስራ ከጀመሩ ጥቂት ጊዜ በመሆናቸውም ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ተናግሯል።
ወጣቱ 80 እና ከዚያ በላይ የሚጠጋ በሬ በማድለብና በግ በማሞከት ላይ መሆኑን በመስክ ምልከታው የታየ ሲሆን የገቢ አቅማቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን አብራርቷል።
ወጣቱ በሬ ከማደለብና ገበያ ላይ ባለፈ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመግዛት ለአካባቢው ግልጋሎት እንዲሰጥ እንዳደረገም ጠቁሟል።
ወጣት በላቸው በአሁኑ ሰዓት በመስክ ካለው ንብረት በተጨማሪ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እንዳለው ተናግሯል።
ወጣቱ ከዚህ በበለጠ ተግባሩን ለማጠናከር የከብት ማደለብያ ቦታና የገበያ ትስስር ችግር እንዳጋጠመው ተናግሮ የሚመለከተው አካል ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቋል
