





የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘውን የወልደሀኔ-ዱርጊ የመንገድ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።
የወልደሀኔ – ዱርጊ መንገድ ስራ ፕሮጀክት 41 ኪሎ ሜትር እርዝማኔ ያለው ሲሆን በ2015 ዓ/ም ወደ ግንባታ መግባቱ ይታወሳል።
የመንገድ ግንባታ ሂደቱን የጎበኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ግንባታው በተያዘው ጊዜ እንዲጠናቀቅ አጠቃላይ ስራው መፋጠን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
የመንገድ ግንባታው የሚከናወንበት አከባቢ በቂ የግንባታ ግብዓት ያለበት እንዲሁም ከሶስተኛ ወገን የወሰን ማስከበር ነጻ የኾነ በመሆኑ ተቋራጩ በሙሉ አቅም እንዲሰራ አሳስበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በፕሮጀክቱ ከወልደሀኔ እስከ ኦሞ ወንዝ ያለውን አጠቃላይ ግንባታ ሥራ ከሌሎች የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች ጋር በመኾን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
