የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል በቢፍቱ ከተማ አስተዳደር ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ መቱ አኩ በመክፈቻ ንግግራቸው የውይይቱ ዋና አላማ የህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ መሰረት ያደረገ እንደሆነ በመግለፅ ሀገራችን በመደመር መንግስት እሳቤ በመመራት በርካታ ውጤቶችን እያስመዘገበች ትገኛለች በማለትየመደመር መንግስት ከህዝብ የተወለደ በመሆኑ ህዝብን በማዳመጥ የተጎደሉ ነገሮች ላይ ቤተሰባዊ ውይይት በማድረግ የሚመልስና የሚፈታ ነው ብለዋል።

አክለውም አቶ መቱ አኩ የጉባ ብስራቶች የኢትዮጵያ የታሪክ እጥፋት እየቀየረ ሀገራችንን ቀና እያደረገ መሆኑን ገልጸው የመንግስት ኢንሸቲብ የሆነውን የቱሪዝም ፣የግብርና እንዱሁም ሌሎች ተግባርን በከተማ አሰተዳደሩ እውን ለማድረግ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የቢፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኦሚስ ከሲከራ እንደገለፁት በአለም አቀፍ ተወዳዳሪዎች ሀገር ለመምራት በየደረጃ ያለውን ህዝብ ማዳመጥ ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስለትውልዱ የተሻለች እና ተምሳለት የሆነች ሀገር፣ክልልና ዞን ብሎም ከተማን ለማስረከብ ህዝብ፣መንግስትና ፓርቲ በተቀናጀ መልክ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፍርዳወቅ አለሙ በወቅታዊ ሀገራዊ ክልላዊ ዞናዊና ከተማዊ ጉዳዮች በተመለከተ ሰነድ እያቀረቡ መሆናቸዉን የጉራፈርዳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *