በቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ በአቶ ጌዲዮን ኮስታብ የተመራ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎችና የአመራር ቡድን በጉራፈርዳ ወረዳ በርጂ ቀበሌ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኙ።

Spread the love

በቀበሌዋ የታዩ የልማት ስራዎችና የተቋማት የግንባታ ሂደቶች ለሌሎች መዋቅሮች ተሞክሮ የሚቀመርበት ነው ብለዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ በአቶ ጌዲዮን ኮስታብ የተመራ የዞን ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋናና ምክትል አፈ ጉባኤዎች ፣ የቋሚ ኮሚቴ አባላት በወረዳው በርጂ ቀበሌ በመገኘት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ በቀበሌው የምክር ቤት አባል በሆኑት በአርሶ አደር ዳምጠው ካስዬ በበጋ መስኖ የለማ የሽንከርት ማሳ ተጎብኝቷል። አርሶ አደሩ በጉብኝቱ እንደተናገረው ከአርሶ አደር ተከራይቶ በሚሰራበት 2 ሄክታር ማሳ ላይ ሽንኩርት በመስኖ እያለማ መሆኑን ተናግሯል።

ዝዋይና መቂ ድረስ በመጓዝ የቲማቲም ፣ ሽንኩርትና የተለያዩ የጓሮ አትክልት ልማት ላይ ልምድ ቀምሶ በመመለስ ወደ ልማት መግባቱን ገልጿል። አሁን ካለበት የመሬት ችግር አንጻር በሚፈልገው መልኩ ለመስራት መቸገሩን ገልጾ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

በቀበሌው የግብዓት ማስቀመጫ መጋዘን ፣ የግብርና ባለሙያዎች ማደሪያ ፣ የቢሮና መሰል ግንባታዎች በህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተሰራ መሆኑም በጉብኝቱ ምልከታ ተደርጓል።

ሌላው በቀበሌው በጸሐይ ግባት መንደር ነዋሪ የሆነው የአርሶ አደር መኮንን አራጋው ዘመናዊና የጨፈቃ ቀፎ የንብ ማነብ ስራ የተጎበኘ ሲሆን አርሶ አደሩም አሁን ላይ ከ40 በላይ ቀፎ ይዞ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በባህላዊ መንገድ ሲያንብ ውጤታማ እንዳልሆነ ገልፆ በወረዳው ባለሙያዎች ስልጠና በማግኘቱ አሁን ላይ ባህላዊ ቀፎዎችን በጨፈቃና በዘመናዊ ቀፎ እየቀየረ መሆኑን ገልጿል። በግብርና ባለሙያዎ እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍም ውጤታማ እያደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ጌዲዮን ኮስታብ ከጉብኝቱ በኀላ እንደተናገሩት በቀበሌው በበጋ መስኖ የሽንኩርት ልማትና በኩታ ገጠም የቦቤ ልማት ስራ ለሌሎች መዋቅሮች ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል። በንብ ማነብ ስራም አርሶ አደሩ ከባህላዊ ወደ ጨፈቃና ዘመናዊ ቀፎዎች ሽግግር እያደረገ ያለበት ሂደት የሚደነቅ ነው ብለዋል። የ

የምክር ቤቶች የምክክር መድረክ ዋና አላማውም አንዱ ከሌላው መዋቅር ልምድ እንዲቀስምና እንዲሰፋ ማድረግ መሆኑን ገልጸው ውጤቱም በተጨባጭ እየታየ መሆኑን ገልጸዋል ሲል የቤንች ሸኮ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *