ሁለንተናዊ ተቋማዊ አቅም በማቀናጀትና በመረባረብ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን መታገል ይገባል ፦ የኮሚሽኑ አመራሮች

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት እና የክልሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መካከል ብልሹ አሰራርንና ሙስናን ለመታገል በትብብር ለመስራት መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የመደመር ሳንካ የሆኑት ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በጽኑ አቋም በመታገል ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መረባረብ አለብን ብለዋል።

የስምምነት ሰነዱ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማሳለጥ ውጤታማ የሆነ የሙስናና ብልሹ አሰራሮች ላይ ማዕከል አድርጎ በጥብቅ ዲስፕሊን እና በተጠናከረ መልኩ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለፀረ ሙስና ትግሉ የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት፣ ጥናት ላይ ተመስርቶ ሙስናን መከላከል እና መረጃዎችን መለዋወጥ ፣ የትውልድ ስነ ምግባር ግንባታው ላይ በጋራ ተቀናጅቶ መስራት የኮሚሽኖች የስምምነት አንኳር ጉዳዮች እንደሆነ ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ ገልጸዋል።

በመግባቢያ ሰነዱ የክልሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ አይበራ እንደገለጹት በየደረጃው ያለው አመራር፣ባለሙያና ህብረተሰቡ በሙስናና ብልሹ አሰራሮች ላይ የተቀናጀ ትግል በማድረግ የተጀመረውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ መረባረብ ይገባል።

ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ተቋማት ሁለንተናዊ አቅም በማቀናጀት በመረባረብ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣትና የህብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

በተቀናጀና በተደራጀ ሁኔታ ሙስናና ብልሹ አሰራር በመከላከል የሀገራችንን እና የክልሉን ሁለንተናዊ ብልጽግና እንዲረጋገጥ ሁሉም አመራርና ባለሙያዎች በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

በመንግስት በህዝብ መካከል ሆኖ በህገ ወጥ ተግባር ላይ የተሰማራውን ሀይል በተቀናጀ መንገድ ተጨባጭነት ያለው የሙስና መከላከል በመስራት እንዲነጠል ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል በየደረጃው በተደረገ የተቀናጀ ጥረቶች በርካታ ውጤቶች የተመዘገበ መሆኑን ገልጸው ይህን የተቀናጀ ጥረት የመንግስትና ህዝባዊ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በቁርጠኝነት መታገል ይገባል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ያዙ እንደገለጹት በፀረ ሙስና ትግል ላይ በጋራ አቋም ከሰራን ፓርቲያችን ያስቀመጣቸውን ግቦች ለማሳካት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

ሙስናና ሌብነት የብልጽግና ፓርቲ ቀይ መስመር በመሆኑ እነዚህን ብልሹ አሰራሮችን ከምንጩ ለማድረቅ አመራሩና ባለሙያው በጽኑ አቋም መታገል እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

በየደረጃዉ የሚገኙ አባላትና አመራር በፕሮግራም፤ በመተዳደሪያ ደንብ እና በዲስፒሊን መመሪያ የተቀመጡ የፀረ-ሙስና ትግል አቅጣጫዎች ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ የፀረ-ሙስና ህጎችና አሰራሮች ግንዛቤ ኖሯቸዉ ተልዕኳቸዉን በብቃትና በቁርጠኝነት መወጣት ይጠበቃል ብለዋል ።

የክልሉ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ሰብሳቢ ወ/ሮ ራሄል ለዊ እንዳሉት ጠንካራ ኮሚሽንና ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የፀረ ሙስና ትግሉ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው በቁርጠኝነት መስራት አለብን ብለዋል።

ሌብነትን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር አመራሩ የመሪነት ሚናውን መወጣት እንዳለበት አክለው ገልጸዋል።

በመግባቢያ የስምምነት ሰነዱ ላይ የክልሉ ስነ ምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽነሮች ፣የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣የክልሉ የኮሚሽን አመራሮች፣የክልሉ የህብረት ኮሚሽን ኮሚቴ አባላት፣የዞን የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *