ፀጋዎቻችን ወደ ሃብት በመቀየር እና በአግባቡ ለመጠቀም በመፍትሔ ላይ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

Spread the love

በምዕራብ ኦሞ ዞን የክልሉ የሱፐርቪዥን ቡድን በፓርቲ እና በመንግሥት ሥራዎች ዙሪያ የድጋፍ እና ክትትል ሥራ ጀምሯል።

በመድረኩ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደተናገሩት በባለፈው ግማሽ አመት ዉስጥ የተሰሩ የመንግስት እና የፓርቲው ሥራዎች በመገምገም ከግምገማው በሻገር የመስክ ምልከታ እንደሚያደርጉ ነው።

አክለው በመንግሥት እና በፓርቲው መከናወን ያለባቸው ግን ያልተሰሩ የልማት እና የመሰረተ ልማት እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ለ15 ተከታታይ ቀናት የድጋፍ እና ክትትል ሥራዎች እንደሚያደርጉ አቶ ነጋ ተናግረዋል።

ያሉን ፀጋዎች በአግባቡ ለመጠቀም ያሉት ችግሮች መፍትሔ በማስቀመጥ ፀጋዎች ወደ ሃብት ቀይረን ለመጠቀም ጠንክረን መስራት እና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ተደጋግፈን ክልሉ እና ዞኑ ለማሻገር የድጋፍ እና የሱፐርቪዥን ሥራዎች ተጠናክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የተጀመረው የከተማ እና የገጠር የኮሪደር ልማት ሥራዎች በድጋፍ እና ክትትል ላይ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ተጠቅሷል።

በመድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸዉ ኬኒ በበኩላቸው በኢኮኖሚ በማህበራዊ እና በአስተዳደር ዘርፍ የሚደረገው ድጋፍ እና ክትትል ሥራዎች በመጀመሩ ለቀጣይ ዉጤታማ ሥራ እንደሚሰራ ተናግሯል።

በድጋፋዊ ክትትል ላይ የሚነሱ ክፍተቶች በአግባቡ ለይተው የቀጣይ የእቅድ አካል ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸው አስገንዝበዋል።

የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ በድሉ መዓዛ በዞኑ በባለፉት 6ወራት ዉስጥ በመንግሥት እና በፓርቲው የተሰሩ ሥራዎች በሪፖርት አቅርበው ዉይይት ተደርጎበታል።

የክልሉ የድጋፍ እና የሱፐርቪዥን ቡድን ከዞኑ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *