




መድረኩ “ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ ፓርቲው በሁሉም ዘርፍ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ለጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ ጠንካራ ኢንስፔክሽን ያለው ሚና ከፍተኛ ስለመሆኑ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ኮሚሽኑ በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች ስላከናወናቸው ተግባራት አድናቆታቸውን የገለጹት አቶ በላይ ፤ በቀጣይ እነዚህን ጅምሮች እያላቁ ውጤታማ ለመሆን የሁሉም ትብብር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
ብልሹ አሰራርን ከማስወገድ፣ ሀብትን ከብክነት ከመከላከልና የአስተዳደር ሥርዓትን ከማዘመን ረገድ ኮሚሽኑ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አመላክተዋል።
የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ወይዘሮ ራሄል ሌዊ በበኩላቸው ፤ በክልሉ አስፈላጊው የድጋፍና ክትትል ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ተግባራትን በኃላፊነትና በቁርጠኝነት ከማከናወን ረገድ የተጀመሩ እንቅስቃሰዎች የተሻለ ውጤት የታየባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለቀጣይ ግቦች ተግባራዊነት ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በውይይት መድረኩ የሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ባለድርሻ አካላት መገኘታቸዉን ደሬቴድ ቦንጋ ቅርንጫፍ ዘግቧል።
