የዕቅድ ክትትልና ግምገማ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ያለመ የሥራ ጉብኝት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ተጀመረdcs

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የእቅድ አፈጻጸምና የልማት ፕሮጀክቶች አስተዳደርን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን እና ለማጠናከር ያለመ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ በፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የተመራ የፌደራል ልዑክ ቦንጋ ከተማ ገብቷል።

የልዑካኑ ጉብኝት ዋና ዓላማ የክልሉን የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ግልጽ፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ የሚያስችል ዘመናዊ የዲጂታል እቅድ ክትትልና ግምገማ ስርዓትን በተግባር ላይ ለማዋል የሚያስችል የድጋፍና ክትትል ሥራዎችን ማከናወን ነው።

ልዑኩ ቦንጋ ከተማ ሲደርስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።

በቆይታቸውም ዶ/ር ፍፁም የሚመሩት ቡድን ከክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በመሆን በፕሮጀክቶች አስተዳደር ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደርጋሉ።

ይህም የክልሉን አቅም በመገንባት የዕቅድ ክትትልና ግምገማ ሥራዎችን ወደ ቴክኖሎጂ በማሸጋገር ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት አካል መሆኑ ተገልጿል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *