ነዋሪዎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ሁለተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሥራት ከባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ተባለ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የከተማ ሴፍትኔት ሥራ ፕሮጀክት(UNSNJP) እና የመንግስት ተዛማጅ ፈንድ(GME) የ2016/17 አፈጻጸም ሪፖርትና የ2017/18 ጠቋሚ ዕቅድ ላይ የክልሉ ስተሪንግ ኮሚቴ በሚዛን አማን ከተማ ውይይት አካሂዷል።

የሴፍትኔት ፕሮግራሙ አቅመ ደካሞችን በከተማ ግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በከተማ ቆሻሻ ማፅዳት፣ በአረንጓዴ ልማትና በሌሎች የአካባቢ ልማት ስራዎች ከግንዛቤ እስከ ምርት ድረስ እየደገፈ መሆኑ ተጠቅሷል።

መድረኩን የመሩት የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር የማታለም ቸኮል: የከተማ ሴፍትኔት ፕሮግራም ሚዛን አማን እና ቴፒ ከተሞችን በማቀፍ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ስራዎች ሲከውን መቆየቱን ገልጸዋል።

ፕሮግራሙ የአቅመ ደካሞችን ህይወት ለመለወጥ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአገልግሎት እና ሌሎች አካባቢ ልማት ዘርፎች በማሰማራት ከ16 ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ኃላፊው አክለዋል።

መንግስት ከአጋር አካላት ጋር ጠንካራ ስራ ሠርተው የሚያመጣውን ሀብት ለተፈለገው አካል ከነተጠያቂነት ማድረስ ያስፈልጋል ያሉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ተጠሪ ተቋማት ተግባራትን በቁርጠኝነት መደገፍ አለባቸው ብለዋል።

የፕሮግራሙን አፈጻጸም በዝርዝር ያቀረቡት የቢሮ ምክትልና የከተሞች ማስፈፀም አቅም ግንባታና አካባቢ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አክሊሉ ተገኝ በ1ኛ እና 2ኛ ዙር የህይወት ክሂሎት ስልጠና በመስጠት በተለያዩ የአካባቢ ልማት ስራዎች እንዲሰማሩ ተደርገው ውጤታማ ሆነዋል ብለዋል።

ፕሮግራሙ በሁለቱም ዙር በከተማ አካባቢ የሚኖሩ አቅመ ደካሞችን በተለያዩ የኑሮ ማሻሻያ ስራዎች ላይ ግራንት ሰጥው በማሸጋገር በ3ኛው ዙር በመንግስት ተዛማጅ ፈንድ አስደግፈው 58% የሚሆኑት ሴቶችን ጨምረው ለተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረጉን አመላክተዋል።

በውይይት ወቅት አስተያየት የሰጡት የኮሚቴ አባላት የሴፍቲኔት ፕሮግራሙ አቅመ ደካማ ዜጎችን ከመደገፍ ባሻገር በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ላይ አወንታዊ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ጠቅሶ ፕሮጀክቱ ነዋሪዎችን ደግፈው ካሸጋገራቸው በኃላ የክትትሉን ስራ ማጠናከር ከባለድርሻ ይጠበቃል ብለዋል።

በመጨረሻም የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት 2017/18 ጠቋሚ ዕቅድ ቀርበው ፕሮግራሙ በምግብ ዋስትና ላይ የሚያበረክተውን ለውጥ ተጨባጭ በማድረግ ዙሪያ አቅጣጫ አስቀምጠው አጠቃለዋል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *