





ግምገማው በዋናነት በመደበኛ በፓርቲ ስራዎችና በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ የተቀመጡ ሀገራዊ 6ቱ የትኩረት አቅጣጫ ግቦችን ስኬታማ ለማድረግ በዞኑ እየተሰራ ያለው አፈጻጸም በጥንካሬና በጉድለት በመገምገም ተግባራቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ሰሌዳ ስኬታማ ለማድረግ ታሳብ ያደረገ ነው።
ለግምገማ መድረኩ የተዘጋጀውን የዞኑን ወቅታዊ አፈጻጸም ሪፖርት የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታከለ ታምሩ እያቀረቡ ይገኛል ።
በመድረኩ ላይ የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ፣ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ የሽዋስ ዓለሙ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ያዙ እና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ መኩሪያን ጨምሮ የካፋ ዞን አስተባባሪ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል ።
