
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ዛሬ ከኔዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀንኬ ብርነስ ሰዋት ጋር ውይይት አድርገዋል።
ውይይታቸው የሁለቱ አገራትን ግንኙነት እና ትብብር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።
አምባሳደር ታዬ በወቅቱ እንዳሉት የኔዘርላንድ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በልማት ትብብር፣ በኢንቨስትመንት እና በሰብአዊ ዕርዳታ ድጋፍ መስክ ያለውን ትብብር አድንቀዋል።
ተጨማሪ ትብብሮችን ለማጎልበት በሚያስችሉ የኢኮኖሚ መስኮች አብሮ መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል።
የኔዘርላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ጠንካራና ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክራ ለመቀጠል እንደምትፈልግ ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ ከ100 በላይ የኔዘርላንድ ኩባንያዎች በኢንቨስትመንት መሰመራታቸውን በማንሳት፥ በንግድና ኢንቨስትመንት የበለጠ ለመተባበር የአገራቸው ፍላጎት መሆኑን ገልፀዋል ።
ቀጠናዊ እና አለምአቀፋዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አብሮ ለመስራትም ሁለቱ ሚኒስትሮች ሃሳብ መለዋወጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
