በመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የ1445ኛዉ የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም እንዲከበር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ::

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽር ሰብስቤ ሻዎኖ እንደገለፁት በመላ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በክልሉ ሁሉም ዞኖች፤ከተማ አስተዳደሮች እና ወረዳዎች በሰላም እንዲከበር የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ስራ መግባቱን ገልፀዋል፡፡

በዓሉን ተከትሎ ሊደርሱ ከሚችሉ የትራፊክ አደጋና ሊከሰቱና ሊፈጠሩ ከሚችሉ የእሳት ቃጠሎዎች ሁሉም ሰው እራሱንና ሌሎችን ሊጠብቅ እንደሚገባም አስታውቋል::

የ1445ኛዉ የኢድ አልፈጥር ሰላት በሚሰገድበት ስፍራ እና ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ የተጠናከረ ጥበቃ እንደሚደረግ የገለፁት ኮሚሽነር ሰብስቤ በዓሉ በሰላም እንዲከበር የፀጥታ መዋቅሩ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱንም አስረድተዋል፡፡

ስለሆነም ለበዓሉ በሰላም መከበር ህዝበ ሙስሊሙና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከፖሊስና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር እንዲተባበሩና ተገቢውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርበዋል፡፡

ህዝቡ በራሱ ሰላሙን መጠበቅ እንዳለበት ገልፀው በዓሉን የሚያውኩ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲያስተውል በአቅራቢያው ለሚገኘው የፀጥታ አካል መረጃና ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ለኢድ አል-ፈጥር በዓል አደረሳችሁ በማለት በራሳቸውና በመላው የፖሊስ አባላትና አመራሮች ስም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *