




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ምክር ቤት በታርጫ ከተማ እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ያቀረባቸው የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ላይ ሹመት ምክር ቤቱ ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አአድቋል።
በዚህም መሠረት
1-አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ:-የክልሉ ሰው ሀብት ልማትና ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ
2ኛ -ረዳት ፕሮፌሰር ዘመድኩን ሰለሞን :-የኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ኃላፊ
3ኛ -አቶ መቱ አኮ የክልሉ ቆላማና እና አርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
4-አቶ ታሪኩ አካሉ የክልሉ ንግድና ኢንቬስትመንትን ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ እንዲሁም ሌሎች የተሸጋሸጉትን በዝርዝር አቅርበው ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
በፍቅር ከበደ
