በየደረጃው ድጋፍና ክትትል በማጠናከር የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ የሚቆጠርና የሚጨበጥ ውጤቶችን ማስመዝገብ ይጠበቃል ፦አቶ ፍቅሬ አማን

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በተገኙበት በካፋ ዞን ከዞን ማዕከል እስከ ቀበሌያት ድረስ የተከናወኑ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ግብረመልስ ተገመገመ።

በግምገማዉ ወቅት አቶ ፍቅሬ አማን፤ የድጋፍና ክትትል ዓላማዉ የተጀመሩ ሥራዎችን የበለጠ ማላቅና የሚታዩ ክፍተቶችን በፍጥነት ለመፍታት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ነው ያሉት።

ለዚህም በየደረጃው ጠንካራ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ለብልጽግና ጉዞ ጠንካራ መሠረት የሚጥሉ የሚቆጠርና የሚጨበጥ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደሚጠበቅ ነው አቶ ፍቅሬ አማን የገለጹት።

በስንዴ ልማትና በሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት በመስጠት የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ እንዲሁም የግብርናና ገጠር ትራንስፎርሜሽን ሽግግር ውጤታማ እንዲሆኑ ተግባራት በልዩ ትኩረት መመራት አለባቸው ነው ያሉት።

ለቱሪዝም እመርታ በየአካባቢው የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን ማልማት ይገባል ያሉት አቶ ፍቅሬ አማን፣ በከተማና ገጠር ኮርደር ልማት ሥራዎች ትኩረት በማድረግ አካባቢዎች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ መሥራት ያስፈልጋልም ብለዋል ።

በየደረጃው አደረጃጀቶችን በማጠናከር በስራ ዕድል ፈጠራ፣ የእርሻ መሬቶች ጾም እንዳያድሩ መሥራት፣ ዕዳዎችን ዜሮ ማድረግ፣ በገቢ አሰባሰብና በሌሎች የፓርቲና መንግሥት ንቅናቄ እና መደበኛ ተግባራት ላይ በተጠናከረ እንዲሰራም አመላክቷል።

በህዝባዊ ውይይት መድረኮች ከማኅበረሰቡ የተነሱ ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱ የዕቅድ አካል ተደርጎ ይሰራሉ ያሉት አቶ ፍቅሬ አማን የሚፈጸሙ ተግባራት ውጤታማነታቸው እንዲረጋገጥ አመራሩ ሥራዎችን በቁርጠኝነት በየጊዜው መከታተልና መቆጣጠር እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *