የደቡብ ዕዝ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው

Spread the love

በሀገር መከላከያ ሰራዊት የደቡብ ዕዝ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በባቱ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

በኦሮሚያ ክልል ባቱ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የምስረታ በዓል ላይ የኢፌዴሪ የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የፌዴራል እና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ አባገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *