ሁለተኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ ሰልጣኝ አመራሮች የቦንጋ ከተማ የከተማ ኮሪደር ልማት እየጎበኙ ነዉ

Spread the love

”በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል ሃሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ2ኛ ዙር በሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ ሰልጣኝ አመራሮች በቦንጋ ከተማ እየተሰራ ያለውን የከተማ ኮረደር ልማት ሥራ እየጎበኙ ይገኛሉ።

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረዉ የከተሞች ኮሪደር ልማት ከተሞችን በማስዋብ ገጽታቸውን እየቀየረ ይገኛል።

የቦንጋ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ ተክለዓብ ቡሎ(ዶ/ር) ለጎብኚዎች ስለቦንጋ ከተማ ኮሪደር ልማት የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለጻ አድርጓል።

መንግስት ከተሞችን ለማስዋብና የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል አትኩሮ እየሰራ ካለው ሥራ አንዱ ኮሪደር ልማት እንደሆነ የቦንጋ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ኃላፊና የኮንስትራክሽን ዘርፍ ኃላፊ ኣንጂነር ሣራ አክሊሉ

ገልጸዋል።

በቦንጋ ከተማ በባለፈዉ ዓመት አንድ ኪሎ ሜትር የከተማ ኮሪደር ልማት መሰራቱን እና በዘንድሮ ዓመት 34 ኪሎ ሜትር ወሰን በማስከበር 2.34 ኪሎ ሜትር ኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ እንዳለ ጠቅሰዋል

ለሥራው አጠቃላይ 231 ሚሊዮን ብር ተበጅተው ሥራውን በተያዘለት ጊዜ በጥራት አጠናቅቆ ለማስረከብ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኮሪደር ልማቱ 18 ተቋራጮችን የያዘ መሆኑንና ለ500 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩንም ተናግረዋል፡፡

የኮሪደር ልማቱ የአረንጓደ ውበት፣ ስማርት ፖል እና የፍሳሽ ማስወገጃ ያካተተ ሲሆን ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆን ተደርጓልም ብለዋል፡፡

ስልጠኝ አመራሮቹ ከከተማ ከኮሪደር ልማት ሥራዎች በተጨማሪ ሌሎች ልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።

ከስልጠናው በተጓዳኝ የሚደረገው የልማት ሥራዎች ጉብኝት አመራሮች በተለያዩ አከባቢዎች የሚሰሩ ልማት ሥራዎችን በመጎብኘት ልምድ ልውውጥና ተሞክሮ ለመቀመር ያግዛል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *