




ዛሬ ላይ በጊንቦ ወረዳ የዑፋ የዶሮ እንቁላል እና የማር መንደር በተደረገዉ ጉብኝ የክልሉ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራን ጨምሮ የክልል፣የዞንና የወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል።
የጊምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትብብሩ አሰፋ እንዳብራሩት፣የመንግሥት የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭን በመተግበር ገበያን የማረጋጋት እና አቅም የሌላቸውን ወገኖች በማደራጀት የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው።
እንደሳቸው ገለፃ በወረዳው በዶሮ እንቁላል ከተደራጁት በቀን ከ1ሺህ 5መቶ በላይ እንቁላል እየተሰበሰበ ገበያን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የጨራባ ቀበሌ የማር መንደር ያለው የማር ምርት የኮምፖስት አዘገጃጀት ፣የጓሮ አትክልት እና ሌሎችም የልማት እንቅስቃሴዎችም ተጎብኝቷል።
በካሳሁን አሰፋ
