ሠልጣኝ አመራሮች በጊምቦ ወረዳ በውሽውሽ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ

Spread the love

‘በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል ሃሳብ ላለፉት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ላይ የነበሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 2ኛዉ ዙር ሀገር ዓቀፍ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በጊምቦ ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኘ ነው።

በጉብኝቱ በግል አልሚ ባለሀብ አቶ ድንቃለም አደመ እየለማ ያለ የወተት ላሞችን፣ የማታፓ ምቺት የቡና ኢንዱስትሪ እና በአርሶ አደሮች እየለማ ያለውን የሻይ ተክል ተዟዙሮ እየተመለከተ ይገኛል።

በጉብኝቱ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማን ጨምሮ የክልል፣የካፋ ዞን አመራሮች እና ሰልጣኝ አመራሮች ተሳትፈዋል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *