የዘንድሮው የአለም የቱሪዝም ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለ3ኛ ጊዜ“ቱሪዝም ለሠላም ” በሚል መሪ ቃል በቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ

Spread the love

የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዮት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም 45ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ37ኛ ጊዜ እና በክልላችን ለ3ኛ ጊዜ የሚከበርው የቱሪዝም ቀን ‹‹ቱሪዝም ለሰላም›› በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የቱሪዝም አለኝታ ጥናታዊ ጽሁፍ የውይይትና የንቅናቄ መድረክ የሚሳተፉበት ከፌዴራል እና ከክልሉ ሁሉም ዞኖች የመጡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በካፋ ባህል አዳራሽ ተገኝተዋል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕስ መስተዳደር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማማሞ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዮት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽን ጨምሮ የፌዴራል፣ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉም ይሆናል፡፡

የክልሉ የቱሪዝም መዳረሽ አለኝታና ተግዳሮቶች፣ የቱሪዝም ፓኬጅና መዳራሻ ካርታ ጥናታዊ ጽሁፍ፣ የባህል ምግብ ዝግጅት ጥናታዊ ጽሁፍ፣የኢግዜቨሽንና ባህላዊ ምግብ ዝግጅት ቅምሻ የሚደረግ ፣ የቱሪዝም ሀብቶች ሰነድ ፣ የቱሪዝም ንቅናቄ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ማድረግ መድረኩ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *