አደረጃጀቶች የሕዝብን የሰላምና የልማት ጥያቄ ለመመለስ ፋናወጊ ሆነው ሊንቀሳቀሱ ይገባል፦የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ፍቃዱ ተሰማ

Spread the love

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት “የጠንካራ አደረጃጀት ትጋት ለአገራዊ ህልሞቻችን ስኬት” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረውን የ2017 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያና የስራ መመሪያ የሰጡት በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ፍቃዱ ተሰማ አደረጃጀቶች ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ እንዲሁም ልማትን በማረጋገጥ ሚናቸውን በመለየት እስከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ድረስ ንቅናቄ ፈጥረው መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል፡፡

በግዝፈታችን ልክ በውጤት በማጀብ በየወቅቱ በሚካሄድ የግምገማና ምዝና ሂደቶች ተጨባጭ ማስረጃዎችን በተደገፈ መልኩ ማስኬድ እንዲሁም በትግል መምራት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ከላይ እስከታች ባለው የአደረጃጀት መወቅር የሴቶችና የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ የአገራችንን ብልጽግና እውን መሆን ድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል መመዘኛ መስፈርቱን የሚያሟሉ አባላት ምልመላ እና ጥራት ማስጠበቅ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አንስተዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ኃላፊ ክቡር አቶ ካለድ አልዋን በበኩላቸው በክልሎች መካከል የሚስተዋለውን የአፈጻጸም ዥንጉርጉርነት ለማስተካከል በመድረኩ የተገኙ ልምዶችን በመቀመርና በማስፋት በአገር አቀፍ ደረጃ ተቀራራቢ ውጤት ለማስመዝገብ መግባባት መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የአባላትን ስነ ምግባር በማስጠበቅ ተልኮውን በብቃት መወጣት እንዲችል አቅም ግንባታ በየወቅቱ ማካሄድ እንዲሁም የፓርቲው አሠራሮችን እንዲከበሩ ማድረግ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ከስራ አፈፃፀም ግምገማ በተጨማሪ በተለያዩ የፓርቲው የአሰራርና የአደረጃጀት መመሪያዎች ላይ ውይይት በማካሄድ ተጨማሪ ግብዓቶችን በመውሰድ የማዳበር ስራ ተከናውኗል። በመጨረሻም በክልሉ እየተካሄዱ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎች ተጎብኝተው መድረኩ ተጠናቋል።

#Prosperity

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *