በበጀት ዓመቱ 9 ወራት የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራት መከናወናቸዉን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገለጸ

Spread the love

‎ቢሮው የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ ጋዜጣው መግለጫ ስጥተዋል።

‎መግለጫውን የሰጡት የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ወልደማርያም በዛብህ በኢኮኖሚያዊ፤ በማህበራዊ፥ በመሰረተ ልማትና በፍትህና አስተዳደር ዘርፎች የህብረተሰቡን ሁሉ አቀፍ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፎች ተለይተው ተግባራዊ መደረጋቸውን ጠቁመዋል።

‎ግብርና የክልሉ ትልቁ የኢኮኖሚ አቅም በመሆኑ የአርሶ አደሩን ግንዛቤ በማሳደግ የሜካናይዘናሽን እርሻን በማስፋፋትና የምርታማነት ፓኬጆችን ተግባራዊ በማድረግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የወጪ ምርቶችን ማሳደግ ላይ በተሰራው ስራ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል። በዚህም ላላፊት 9 ወራት ከ625 ሽህ ሄክታር በላይ በማልማት ከ23 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ገልፀዋል። ከዚህም ውስጥ 85 ሺህ ሄክታር የሚሆነው በኩታገጠም የለማ ሲሆን 14 ሺህ ሄክተር በሜካናይዝድ እርሻ መልማቱን ጠቁመዋል።

‎የበጋ ስንዴ ኢኒሼቲቭ በክልሉ በግብርናው ዘርፍ ተጨማሪ አቅም እየፈጠረ መሆኑን ያብራሩት ዶክተር ወልደማርያም በዚህም ላለፉት 9 ወራት ከ5500 ሄክታር በላይ የበጋ ስንዴ መልማቱን ገልጸዋዋል።ምርታማነቱን ለማሳደግ በተወሰደው እርምጃ በሄክታር ወደ 35 ኩንታል ማሳደግ እንደተቻለም ገልፀዋል።

‎ቡና የክልሉ ዋነኛው የኢኮኖሚ መሰረት በመሆኑ ምርታማነትንና የማሳ ሽፋን ለማሳደግ ከፋተኛ ትኩረት መደረጉን ነው ምክትል ሀላፊው በመግለጫቸው ያብራሩት። በዚህም ላለፉት 9 ወራት የታጠበና ያልታጠበ በጥቅሉ 42,823 ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ተችሏል ብለዋል።ከቡና ባሻገር ሻይና ቅመማ ቅመም ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅም በመሆናቸው 42.08 ቶን ቅመማ ቅመም ለማዕከላዊ ገበያ ቀርበዋል ብለዋል። የሻይ ልማትን ለማስፋፋት በተወሰደው እርምጃ 36 ሄክታር አድስ የሻይ ተከላ መከናወኑንም ጠቁመዋል።

‎የሚገጥሙ ውስጣዊ ችግሮችን በራስ አቅም ለመቋቋም የመጠባበቂያ እህል ክምችትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ ከ6684 ኩንታል በላይ እህልና 2120 ሊትር ዜይትን በመጋዘን ለማከማቸት ተችሏል ብለዋል።

‎በስራና ክህሎት ቢሮ ለወጣቶች ስራ ዕድል ለመፍጠር በተደረገው እርብርብ ላለፉት 9 ወራት ከ57 ሺህ በላይ ወጣቶች በግብርና በማኑፋክቸሪንግና በአገልግሎት ዘርፍ የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ በመግለጫቸው ጠቁመዋል። ስራ ዕድል ለተፈጠረላቸው ዜጎች የፋይናንስ አቅርቦትን ለማመቻቸት በተደረገው ጥረት 194 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቆጠብ የተቻለ ስሆን ከመንግሥት ከ658 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መቅረቡን ጠቁመዋል።

‎በኢኖቬሽንና ተክኖሎጂ ቢሮ በተለይ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በዲጂታል መታወቂያ፤የ5 ሚሊዮን ኮደርስና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስፋፋት እንደተቻለ ገልፀዋል። በዚህም ተላላፊ 9 ወራት በዲጂታል መታወቂያ 829 ሺህ 960፤ በመሶብ አንድ ማዕከል ከ25ሺህ 2ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

የዲጂታል መታወቂያና የመሶቦ አንድ ማዕከል አገልግሎት በተለይ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ በማድረግ የዜጎችን የአገልግሎት እርካታን ከማሳደግ አንፃር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል።

‎በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በተለይ ህገወጥ ንግድን በመቆጣጠርና የሰንበትና የምሽት ገበያዎችን በማስፋፋት የዜጎችን የኑሮ ውድነት ለማቃለል ትኩረት መደረጉን ገልፀዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ ላለፉት 9 ወራት 19 የምሽት ገበያዎችና 55 የሰንበት ገበያዎችን በማቋቋም አምራቹን ቀጥታ በሸማቹ ጋር በማገናኘት የዋጋ ንረትን የመቆጣጠር ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

‎በክልሉ ገቢን በማሰባሰብ የወጪ ፍላጎትን በክልሉ ገቢ የመሸፍን ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን በመግለጫቸው ያነሱት ዶክተር ወልደማርያም በበጀት ዓመቱ ላለፉት 9 ወራት ከ14.4 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 12.6 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ጠቁመዋል። አፈፃፀሙ ከአምና ተምሳሳይ ወቅት ጋር ስነፃፀር ከ6.8ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል።

‎የቢሮው ምክትል ሀላፊ ያነሱት ሌላኛው ነጥብ የክልሉን መሰረተ ልማት በማሳለጥ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰጠውን ትኩረት ስሆን በመንገድ፤ በንፁህ መጠጥ ውሃ፥በመስኖ አውታሮችና በድልድይ ግንባታ ተጀምሮ የቆሙትን ማጠናቀቅና አዳድስ ፕሮጀክቶችን መጀመር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

የትራንስፖርት ዘርፉን ለማሳለጥ በተወሰደው እርምጃ የቦንጋ፣የታርጫና የሚዛን መናኸሪያዎች ተጠናቆ በቅርቡ አገልግሎት እንደሚጀምሩ ጠቁመዋል። ለመሰረተ ልማት ግንባታ የህብረተሰብ ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን ጠቁመው ላለፉት 9 ወራት ከህብረተሰቡ ከ300 ሚሊዮን የሚበልጥ ገንዘብ ለመሰረተ ልማት ግንባታ ማዋጣቱን ገልፀዋል።

‎በክልሉ ከማዕድን ዘርፍ የሚገኘው ጥቅምና ዘርፊ ለጥቅል ኢኮኖሚ ያለው አስተዋጽኦ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን ያብራሩት ዶክተር ወልደማርያም ላላፉት 9 ወራት ብቻ ከ302.276 ኪሎግራም ወርቅ ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ ከ40 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት ተችሏል ብለዋል።

‎በማህበራዊ ልማት ዘርፍ በተለይ የትምህርት ስብራትን በመጠገን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተወሰደው ቁርጠኝነት በትምህርት ለትውልድ ኢኒሼቲቭ ከ484 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልና የተማሪዎች ሚገባ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በትምህርት ዘርፉ በተለይ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተሰጠው ትኩረት 61 ሞዴል ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ ሲሆን 30 ትምህርት ቤቶች ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃታቸውን ገልፀዋል።

‎በጤናው ዘርፍ የወባ ስርጭትን ለመቆጣጠር በተለይ የወባ አጎበርና የኬሚካል ስርጭት ስራ ውጤት ማስገኘቱን ጠቁመው በወባ ምክንያት ይፈጠር የነበረው ሞት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ማሳየቱን አብራርተዋል። የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት የጤና ተደራሽነትን እያረጋገጠ በመሆኑ 428,680 አባላት ማፍራት ተችሏል ብለዋል።

‎የሴቶችን ተጠቃሚነት ማሳደግ፤ የባህል ሀብትን ማልማት፤ የቱሪዝም መሰረተ ልማትን ማስፋፋትና በመጥፋት ላይ የሚገኙ ቋንቋዎችን ለይቶ ማሳደግ በማህበራዊ ዘርፍ ከሚሰሩ ተግባራት መሆናቸውን ገልፀዋል።

‎በአስተዳደርና ፍትህ ዘርፍ በተለይ የዜጎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ምንጭ በመለየት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

‎በቀጣይ የሌማት ትሩፋት፤ የከተማ ግብርናና የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቮችን ማጠናከር፤የገቢ አቅምን ለይቶ መሰብሰብ፤የተጀመሩ የካፒታል ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቮችን በልዩነት መፈፀም፤የገጠርና የከተማ ኮሪደር ልማት ስራን ማጠናከርና ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በልዩነት በመቆጣጠር የዋጋ ንረትን መቆጠር የትኩረት ነጥቦች ሆኖ እንደሚተገብሩት ነው ዶክተር ወልደማርያም በመግለጫቸው ማጠቃለያ የገለፁት።

‎በንጉሴ ወልደየስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *