




የክልሉ የምርጫ አብይና ንዕስ ኮሚቴ የእስካሁኑ የተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።
በአብይና ንዕስ ኮሚቴው በእስካሀኑ በቅድመ ምርጫ አተገባበር ዙሪያ የታዩ ጠንካራ ጎኖች እና ክፍተቶች ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።
በምርጫ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ለ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን ምቹነት ለመፍጠርና የተሳካ ምርጫ ለማካሄድ በከፍተኛ ቁርጠኝኘት ስሜት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በዚህም ምርጫው ሰላማዊ፣ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ ተዓማኒና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለውና በፓርቲያችን ብልጽግና አብላጫ ድምፅ እንዲጠናቀቅ የተጀመሩ መልካም ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
አመራሩና አባሉ በቅድመ ምርጫ ፣ምርጫና ድህረ ምርጫ ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ውጤታማ ምርጫ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ታሪካዊ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አመላክተዋል።
ከቀበሌ እስከ ክልል መዋቅር ድረስ በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ ውጤታማ የምርጫ ቅስቀሳ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በእስካሁን የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ በማጥለቅና በማስፋት ክፍተቶችን ከወዲሁ በጊዜ የለንም መንፈስ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የፓርቲውን መንትያ ግቦችን ለማሳካት በግልም ሆነ በጋራ መስራት ይጠበቃል ያሉት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ በዚህም የምርጫ ህጉን ተከትሎ መስራት ይገባል ብለዋል።
