የክልሉ ሱፐርቪዥን ቡድን በሸካ ዞን ድጋፋዊ ክትትል እያደረገ ነው

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ በሆኑት በአቶ በላይ ተሰማ የተመራው የክልሉ ሱፐርቪዥን ቡድን በሸካ ዞን ተገኝተው የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ግምገማ በቴፒ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

‎በቆይታቸው በዞኑ እየተሰሩ ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን እንዲሁም የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም እንደሚገመግምና የተሰሩ ተግባራትን የመስክ ምልከታ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

‎የቡድኑ አስተባባሪና የክልሉ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ የሱፐርቪዥን ዓላማው በበጀት ዓመቱ በፓርቲ ክንፍ የታቀዱ ተግባራትና አፈፃፀማቸውን መከታተል በፓርቲ መሪነት የመጡ ውጤቶችን መቀመርና ተሞክሮ ማስፋፋትና ማስቀጠል እንዲሁም ፓርቲው የያዘውን ‘ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ’ የሚሰሩ ተግባራት እንዲሁም የዞኑን ነባራዊ ሁኔታ በመመልከት በቀጣይ ዕቅዶች ላይ አካቶ ለመስራት ያለመ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

‎በፓርቲ መሪነት በንቅናቄ እየተሰሩ ያሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማነት፣ የፓርቲ አደረጃጀት ቁመና ማጠናከር እንዲሁም የአመራርና አባላት አቅም መገንባት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አብራርተዋል።

‎በቀጣይ ቀናት በተመረጡ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳር መዋቅሮች የተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳር ተግባራት የመስክ ምልከታ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።

‎በውይይቱ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፕላን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ ፣የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ ፣የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ፣የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ አለሙን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *