




በምዕራብ ኦሞ ዞን በጀሙ ከተማ በትምህርት ሚኒስቴር በ557 ሚሊዮን ብር በጀት የሚገነባው አዳሪ ትምህርት ቤት ተጎብኝቷል ።
በጉብኝቱ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ጨምሮ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ ፤ የክልል፣ የዞንና የጀሙ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በቦታው
ተገኝተው ጉብኝት አድርጓል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሆነ በተደረገው ገለፃ መደረጉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
