




ጳጉሜን 4 – የኅብር ቀን “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
ዕለቱን በማስመልከት በቦንጋ ከተማ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በማስ ስፖርት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ሌሎች ሁነቶች ተደርገዋል፡፡
በመረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ጳጉሜን 4 – የኅብር ቀን “ኅብራችን ለዘላቂ ለሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በገራችን በተለያዩ አካባቢዎች እየተከበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ኅብር ማለት የተለያዩ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የሐይማኖት እና የባህል ልዩነቶች ሳይገድበን በኅብር በጋራ የሚንቆምበት ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር፣ ብሔረሰቦች ፣ ማራኪ ውብ ባህል እንዲሁም የተለያዩ ውብ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት መሆኗን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን አያሌ ሀብቶቻችንን በአግባቡ ለሀገር ሠላምና ልማት ማዋል የሚንችለው በጋራ ስንቆም መሆኑን ነው የጠቆሙት፡፡
ለዚህም የረሳችንን ማንነት እየጠበቀን አርበኝነትን በመላበስ በኅብር ሆነን የትላንት ትግላችንንና የዛሬ ጥንካሬያችንን በአግባቡ እየዘከረን ለመጭው ትውልድ ማስተላላፊ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
የካፋ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ እንዳሻው ከበደ በበኩላቸው ስፖርት አንዱ የኑሮ ዘይቤ መሆኑን ጠቁመው ጤንናታችንን ለመጠበቅ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማዘውትር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሀገራችንን ዕድገት ለማፋጠንና ብልጽግናን ለማረጋገጥ አንድነት ወይም ኅብር ከምንም በላይ መሆኑን ገልጸው ለዚህም እያንንዳችን የበኩላችንን አስተዋጽኦ ልናበረክት ይገባል ብለዋል፡፡
በመቀጠልም ጳጉሜን 4 – የኅብር ቀን ከሰዓት በኀለ በተለያዩ ባህላዊና ክንውኖች ተከብሮ የሚውል ይሆናል፡፡
በመረሃ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልል፣የካፋ ዞን፣የቦንጋ ከተማ አመራሮችና የከተማዉ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
