
ሁሉም የኛ በእኛ ለእኛ የተሰጡ ናቸው። ሁሉን እናከብራለን፤ በሁሉም እንኮራለን።
ኅብረ ብሔራዊነታችን መልካችን፣ አንድነታችን ደግሞ ህልውናችን ነው። እነዚህ ኅብራዊ ጸጋዎች በአንዲት ሀገር በኢትዮጵያ የሚገኙ ናቸው። ዓላማችን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ግባችን የኢትዮጵያ ብልጽግና ነው። ይህ ነው አንድነታችን።
የተበታተንን ኅብሮች አይደለንም፤ የተጨፈለቅን አንድ ዓይነቶችም አይደለንም። እኛ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ያለን ኢትዮጵያውያን ነን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
