ተረጂነት ታሪክ፣ አምራችነት መገለጫችን እንዲሆን የገጠር ሽግግር ላይ መሥራት አለብን፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

*********

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በመደመር መንግሥት የዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና ሽግግር፣ ትሥሥር በመደመር መንግሥት በሚለው ሀሳብ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ሽግግር ትሥሥር በመደመር መንግሥት ውስጥ ሦስት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር አንስተው፤ እነርሱም የመጀመሪያው መንደርደሪያ፣ ሁለተኛው መሻገሪያ እንዲሁም ሦስተኛው ደግሞ መስፈንጠሪያ ነው ብለዋል።

የመንደርደሪያው ሀሳብ ዓላማው አቅምን ከችግር ማላቀቅ ሲሆን፣ ግብርና ዋንኛው አቅምን ከችግር ማላቀቂያ መንገድ ነው ብለዋል።

ግብርናውን በአዲስ ዕይታ መምራት ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ግብርናን እንደ መንደርደሪያ የተጠቀምንበት ገና በዘርፉ ያለንን እምቅ አቅም አሟጠን ባለመጠቀማችን ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያላት መሬት እና ውኃ አሁን ካለን የማምረት አቅም በላይ እንድንሰራ ያደርገናል ነው ያሉት።

ተረጂነት ታሪክ፣ አምራችነት ደግሞ የእኛ መገለጫ እንዲሆን የገጠር ሽግግር ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መስራት አለብን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

አርሶ አደሮች አምርተው ለራሳቸው ፍጆታ ከሚያውሉት በላይ ለሽያጭ የሚያቀርቡት እንዲበልጥ መሥራት ይኖርብናልም ብለዋል።

ወቅቱ የሚጠይቀውን የግብርና ቴክኖሎጂዎች መጠቀም፣ ግብርናን ማዘመን፣ ከማምረት እሳቤ ባለፈ ሌሎች የግብርና ዓይነቶችን ማስፋፋት ላይ በትኩረት ከሰራን ግብርናችን በፍጥነት ያድጋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

#EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *