“በህዳሴ ግድብ ምክንያት የግብፅ አስዋን ግድብ አንድ ሊትር ውሃ አልቀነሰም”፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፣ በህዳሴ ግድብ ምክንያት የግብፅ አስዋን ግድብ አንድ ሊትር ውሃ አልቀነሰም።

ህዳሴ ከመመረቁ በፊት ለመረበሽ የሚያስቡ ሰዎች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ህዳሴ ግድብ አልቋል በቅርቡ እናስመርቀለን ብለዋል።

ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያለኝ መልዕክት ህዳሴ ለሱዳን፣ ለግብጽ በርከት መሆኑን ነው ብለው፤ በፍፁም ጉዳት አይመጣባችሁም ሲሉ ተናግረዋል።

ሀገራቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ልማት ልማታቸው መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ወደፊትም ኢትዮጵያ እስከበለፀገች ድረስ የግብፅ ወንድሞቻችንን ጉዳት አናይም ተባብረን ከወንድሞቻችን ጋር ማደግ እንፈልጋለን ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *