የበለፀጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናስረክባለን፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

አጠቃላይ በጀታችን በድህነት ቅነሳ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዚያ የተረፈው ለዕዳ ክፍያ እና ድጎማ ለሚያስፈልጋቸው የሚውል መሆኑን ገልጸዋል።

“አብዛኛው ገንዘባችን ድጎማ፣ ዕዳ ክፍያና መሰል ጉዳዮችን ስለሚያካትት የካፒታል በጀታችን ዕድገት ቢኖረውም ውስን ነው” ብለዋል።

“በአንድ በኩል ኑሮ ውድ ሆነ ደሞዝ ችግር ሆነ እያልን እሱን ሳንመልስ በውስን ገቢ ያገኘውን ገቢ በሙሉ ልማት ላይ ካዋልን ችግሩ ስለሚባባስ ያንን እያስታረቁ መሄድ ያስፈልጋል” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

“የእኛ ዕድገት መታየት ያለበት ስንት ኩንታል እንደጨመርን ነው” በሚል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም እንደነበረው የቁጥር ሳይሆን ጥራት ያለው ዕድገት እያስመዘገበች ስለመሆኑ የሚታይ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚቀጥለው ዓመት ትልቅ ውጤት ያስመዘግባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህ እንዲሆን “ሁሉም ዝቅ ብሎ አፈር እየነካ በትጋት በመስራት፣ ህዝብን በማስተባበር፣ ሌብነትን በመቀነስ፣ በውጤት ማመን፣ ጀምሮ በመጨረስ፣ የኢትዮጵያን ማንሰራራት የሁላችንም እምነት በማድረግ ልማትና ዕድገት ይመጣል” ብለዋል።

ኢትዮጵያ እያደገች፤ እያንሰራራች ነው፤ አቧራዋንና እዳዋን እያራገፈች መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የበለፀጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናስረክባለን ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *