ለአዲዮ ካካ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግምቱ 500 ሺህ ብር የሚጠጋ የደም መመርመሪያ ማሽን ድጋፍ ተደረገ ።

Spread the love

በክልሉ መንግስት የተገዛውን ዘመናዊ የደም መመርመሪያ ማሽን የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አስረክበዋል ።

የክልሉ መንግስት የአዲዮ ካካ የመጀመሪያ ሆስፒታል ሲመረቅ ቃል በገባው መሠረት ለሆስፒታሉ መሠረታዊ የህክምና ቁሳቁስ አስፈላጊ መሆኑን በማመን ይኸው ተገዝቶ ማሽን ድጋፍ መደረጉን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናግረዋል ።

ሆስፒታሉ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ ህብረተሰቡ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምረው ተናግረዋል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለጹት የክልሉ መንግስት በሆስፒታሉ በዕጥረት ከሚታዩ የጤና ግብኣቶች መሠረታዊ የሆነው የደም ምርመራ ማሽን የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት አቅም ይሆናል ብለዋል።

ለዚሁ ዘመናዊ ማሽን ከክልሉ መንግስት 500 ሺህ ብር በሚጠጋ ወጪ መገዛቱን አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል ።

የአዲዮ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገረመው ገብሬ በበኩላቸው ለተደረገው ድጋፍ የክልሉን መንግስት አመስግነዋል ።

ድጋፍ የተደረገው ማሽን በሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይታይ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግር ይቀርፋል ሲሉም ተናግረዋል ።

ለሆስፒታሉ ግብዓት ለማሟላት ቃል የገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ቃላቸውን በመጠበቅ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩም አቶ ገረመው ጠይቀዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *