

የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ የዲዛይን ስራ አልቋል፤ አማካሪ ተቀጥሯል።
ፕሮጀክቱ ሳይጀመር ሙሉ በሙሉ አርሶ አደሮች ቦታቸውን ሲለቁ ኑሯቸው ሳይስተጓጎል አማራጭ ቤት እና የኑሮ ዘዬ እንዲከተሉ ሰፊና እጅግ የሚያኮራ ስራ ተሰርቷል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሁኔታ ለውጪ በረራ የምትጠቀመው የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያን ነው፤ ይህ ደግሞ ወደ ሩቅ ስፍራዎች የሚጓዙ አውሮፕላኖች በቂ የሆነ ነዳጅ ጭነው ሊነሱ አያስችላቸውም። አሁን የመረጥነው ቦታ እነዚያን ችግሮች የሚፈታ ነው።
ከ100 ሚሊየን በላይ ተጓዦችን የሚያስተናግድ ስለሆነ በአፍሪካ የመጀመሪያው ትልቁ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን ትልቁ የአውሮፕላን ማረፊያ ይሆናል።
ኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት ውስጥ ቀዳሚ ሆና አፍሪካን ከተቀሩ አኅጉራት ጋር ለማገናኘት ያላትን መሻት የሚያግዝ ነው።
አውሮፕላን ማረፊያው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያግዝ፣ ኢትዮጵያን ከዓለም ጋር የሚያገናኝ፣ ለአፍሪካም ጥሩ ብስራት ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ነው።
