



ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ “ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ” በሚል መሪ ቃል በከተማዋ ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ አካሄደ።
በተሽከርካሪዎች የታገዘው በዚህ ሰልፍ ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በርካታ ወጣቶችና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተሳተፉት የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ሰለሞን ለዊ እና የከተማው ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት ተጠሪ አቶ አቢዬት ጫራይት እንዲሁም የዞንና የከተማ አመራሮች ለፓርቲው ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።
ሰልፈኞቹ ለፓርቲው ያላቸውን አጋርነትና ድጋፍ የሚገልጹ የተለያዩ መልእክቶችን ያስተጋቡ ሲሆን፣ የፓርቲው የምርጫ ምልክት የሆነውን “የስንዴ ነዶ” በይፋ የማስተዋወቅ ሥራ ተከናውኗል።
የወጣቶች ክንፉ አባላት ፓርቲው የጀመራቸው የልማትና የብልጽግና ጉዞዎች እንዲቀጥሉ ድምፃቸውን ለብልጽግና ፓርቲ እንደሚሰጡና ለዚህም የቅስቀሳ ሥራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በዕለቱ በነበረው መርሐ-ግብር ላይ ገልጸዋል።
